mukerem
Fri, 01/24/2025 - 15:36
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት የ6 ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት የ6 ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እንደገለጹት በአፈጻጸም ላይ የታዩ ድክመቶችን ለማሻሻልና ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ለመቀጠል መድረኩ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
በክልሉ ያለውን የፍትህ ስርዓት ፈጣን ቀልጣፋ ውጤታማ በማድረግ የህብረተሰቡን እርካታ ይበልጥ ለማሳደግ ፍርድ ቤቶች በቅንጅት ትኩረት ተሰጥቶት መስረት ይገባል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የዲጂታል ዳኝነት አገልግሎትን ለማጠናከር ከኢትዮ ቴሌኮምና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ማህበረሰቡ የፍርድ ቤቶችን ገፅታ የሚያበላሹ አካላትን ተጠንቅቆ በፍርድ ቤቶች ያለውን ዕምነትና በጎ አመላካከት እንዲያሳድግም በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
Image
046-55-62-112




