
አቶ መኮንን ተሻለ
የልማት ዕቅድ ክ/ግ/ግ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር
የዳክቶሬቱ ስልክ ቁጥር 0465562021
የዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ተግባርናኃላፊነት
- የሥራ ክፍሉን የተለያዩ የሥራ ቡድኖችን ሥራ ማቀድ፣ ማስተባበር፣ መምራት፣ ውሳኔ በሚያሥፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት፣
- የሥራ ክፍሉን ወይም የሥራ ቡድኖችን የሥራ ውጤት መከታተል፣ መገምገም፣ የእርምት እርምጃ መዉሰድ፣ ግብረ መልስ መስጠት፤ የእቅድ አፈጸጻም ሪፖርት ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ማቅረብ፣
- የሥራ ቡድኖችንና ባለሙያዎችን የአቅም ክፍተት በማጥናት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
- ለዳይሬክቶረቱና ለሥራ ቡድኖቹ የሚያስፈልጉ ግብአቶች እንዲሟሉ ማድረግ፣
- የፖሊሲ ስትራቴጂና የፕሮግራም የፓኬጆችና የፕሮጀክቶች ሀሳቦች ማመንጨት፤ የዶክመንት ዝግጅትና ማሻሻል ሥራውን በመምራት የጸደቀ ዶክመንት ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሰራጭ ማድረግ፣
- ለዘርፉ ሥራ የሚያግዙ የህግ ማእቀፎችን፣ የሥራ መመሪያዎችን፣ ማንዋሎችን፣ ስነ-ስርዓቶችን እና መግለጫዎችን በአዲስ መልክ እንዲወጡና እንዲሻሻሉ ማድረግ፣ የሚዘጋጁትን ሰነዶች ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሰራጩ ማድረግ፣
- የሥራ ዘርፉንና የመሥሪያቤቱን ዕቅድ ዝግጅት፣ አፈጻጸምና የክትትልና ግምገማ ሥራዎች ሊያሻሽሉና ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ የጥናትና የምርምር ሥራዎች እንዲካሄዱ ሀሳብ ማመንጨት፤ማስተባበር፤ የጥናቱን ውጤት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤ ፋይዳውን በመገምገም ሪፖርት ማቅረብ፣
- የመሥሪያቤቱን ስትራቴጂክና አመታዊ እቅድ ማዘጋጀት፤ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤ የክትትልና ድጋፍ፣ የግምገማና ግብረ መልስ ሥራዎችን በኃላፊነት መምራት፣ ማስተባበር፣ በበላይ ኃላፊው እያፀደቀ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣
- የእቅድ ዝግጅትና ሪፖርት፣ የበጀት ዝግጅት፤ የግምገማና እንዲሁም የለዉጥና መልካም አስተዳደር ግብረመልስ ሥራዎች ውጤታማና ቀልጣፋ እንዲሆኑ የአሠራር ስርዓቶችን መዘርጋት፣
- የጸደቀው በጀት ለሥራ ክፍሎች በአግባቡ እንዲደለደል በማድረግ ያሳውቃል አፈጻጸሙን መከታተል፣ መገምገም፣ ግብረ-መልስ መስጠት፣
- የተቋሙንና የዘርፉን የሥራ እቅድና አፈጻጸም የተሳካ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሚደረገው ውይይትና አውደ ጥናቶች ላይ በመገኘት አስፈላጊ ግብአት መዉሰድ፤ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣
- የመሥሪያቤቱን የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የእቅድ ዝግጅት ሥራን እና አፈፃፀምን መከታተል፣ መደገፍ፣ መገምገም፣ ግብረ መልስ መስጠት፤
- የበጀት ዝውውር ጥያቄ ሲቀርብ አግባብነቱን በመመርመር የውሳኔ ሃሳብ ለበላይ ሃላፊው ማቅረብ ሲወሰንም ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤
- የሥራ ክፍሉን ሥራ በተመለከተ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሥራ ግንኙነት ማድረግ፣
- ለበላይ አመራሩና ለተጠሪ ተቋማት ሥራውን በሚመለከት ሙያዊ የምክርና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
- መሥሪያ ቤቱን በእቅድ አፈጻጸምና በጀት አጠቃቀም ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ በማመንጨት ለበላይ ኃላፊው ማቅረብ፣ ሲወሰን ተግባራዊ ማድረግ፣
- የበጀት የዕቅድ ዝግጅትና ግምገማን እንዲሁም የለዉጥና መልካም አስተዳደር ስራዎችን የሚመለከቱ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመር፤ ወደ ሌሎችም እንዲስፋፋ ማድረግ፤
046-55-62-112




