
አቶ ሱልጣን ሙሰማ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ዘርፍ ዳሬክቶሬት
የጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ሥልጣንና ተግባራት
የአስተዳደር እና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ተጠሪነቱ ለፕሬዚዳንቱ ሆኖ የሚከተሉት ዝርዝር ሥልጣን እና ተግባራት ይኖሩታል፡-
ሀ) የክልል ፍርድ ቤቶች አስተዳደራዊ መዋቅር ተጠንቶ እንዲጸድቅ ያደርጋል፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በመመካከር የአስተዳደር ሠራተኞችን ቅጥር ይፈጽማል፣ ይመድባል፣ ያስተዳድራል፣
ለ) የአስተዳደር ዘርፉን የሥራ ሂደቶች እንቅስቃሴና ውጤታማነት በቅርብ ይከታተላል፣ ተገቢውን ድጋፍ ይሰጣል፣
ሐ) የአስተዳደር ሠራተኞችን የትምህርት እና የስልጠና ሁኔታ ያመቻቻል፣
መ) ከበጀት፣ ከመሠረተ ልማትና ሌሎች ሀብቶች እንዲሁም ከሰው ሀብት ጋር ግንኙነት ያላቸውንና በአጠቃላይ ዘርፉንና በዘርፉ ውስጥ ያለውን የአስተዳደር ሠራተኛ የሚመለከቱ ጥናቶች በማድረግ የውሳኔ ሐሳቦችንና ረቂቅ ሕጎችን እንዲዘጋጁ በማድረግ ለፕሬዚዳንቱ ያቀርባል፣ በሚመለከተው አካል ሲጸድቁ ተግባራዊ ያደርጋል፣
ሠ) የዘርፉን አሰራር ለመለወጥ ስልቶችን ይቀይሳል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፣ ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፣ ጉድለት ባጋጠመ ጊዜ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በመመካከር የእርምት እና የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣
ረ) በፕሬዚዳንቱ ተለይተው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
046-55-62-112




