
አቶ ቢኒያም ከበደ
የተከላካይ ጠበቃ ጽ/ቤት ሃላፊ
የተከላካይ ጠበቃ ሥልጣን እና ተግባር
ተከላካይ ጠበቃ ተጠሪነቱ በየደረጃው ላሉት ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡-
- በከባድ ወንጀል ተከሰው የራሳቸውን ጠበቃ አቁመው የመከራከር አቅም ለሌላቸው ሰዎች ወይም በማናቸውም የወንጀል ጉዳይ ፍትህ ይጓደላል ተብሎ ሲታመን ተከሳሽን ይወክላል፤
- የሕግ ምክር አገልግሎት ይሰጣል፣ መልስ፣አቤቱታዎችን፣ የይግባኝና የሰበር ቅሬታዎችን ያዘጋጃል፣ ክርክሮችን ያደርጋል፤
- በማረሚያ ቤት በመገኘት ጥብቅና የቆመለትን ተከሳሽ ወይም ታራሚ ያማክራል፤
- በመከላከያነት የሚያገለግል ደጋፊ ማስረጃ ያሰባስባል፣ያደራጃል፤
- የተከላካይ ጠበቆች ዝርዝር ተግባራት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡
046-55-62-112




