የዋና ሬጅስትራር እና የሬጅስትራር ሥልጣን እና ተግባር
- ዋና ሬጅስትራር ተጠሪነቱ እንደአግባቡ ለሚመለከተው የአቤቱታ መስማትና መወሰን የሥራ ሂደት አስተባባሪ ወይም ለምድብ ችሎት አስተባባሪ ሆኖ በሌላ ሕግ ከተደነገገው በተጨማሪ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
ሀ) የክፍሉን ሥራ በማቀድ ይመራል፣ያደራጃል፣ የማስተባበርና የቁጥጥር ስራን በመስራት ያስተዳድራል፣
ለ) የስራ ድጋፍና ግምገማ፣ የውጤት ምዘና ያካሄዳል፣ ለክፍሉ ስራ አስፈላጊ የሆነ አቅርቦት እንዲሟላ ያደርጋል፣ የእቅድ አፈፃፀም የስራ ሪፖርት ያቀርባል፣
ሐ) የችሎት አስተዳደር ሥራዎች በየዕለቱ መከናወናቸውን ይከታተላል፣ የአሠራር ክፍተት ሲኖር ለሚመለከተው አስተባባሪ ያሳውቃል፣
መ) ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የችሎት አስተዳደር ሥራ እንዲኖር ከሚመለከተው አስተባባሪ ጋር በመነጋገር የተሻለ የአሠራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣
ሠ) ጉዳዩ ከሚመለከተው አስተባባሪ ጋር በመመካከር የቀጠሮ ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲሆን ይሠራል፣
ረ) በሚመለከተው የአቤቱታ መስማት እና መወሰን የሥራ ሂደት ወይም በምድብ ችሎት ለሚገኙ የሬጅስትራር ቡድን መሪዎች የሥራ ስምሪት ይሰጣል፣ ኃላፊነታቸውን በሚገባ ስለመወጣታቸው ይከታተላል፣ ጉድለት ሲኖር ከሚመለከተው አስተባባሪ ጋር በመመካከር ተገቢውን የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
ሰ) በስሩ በሚገኙ ሬጅስትራሮችና የሬጅስትራር ቡድን መሪዎች ወይም ሰራተኞች የሥነ-ምግባር ጉድለት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከተው አስተባባሪ ያቀርባል፣
ሸ) ለሥራው የሚያስፈልጉ የሬጅስትራር ሠራተኞች እንዲሟሉ ለሚመለከተው አስተባባሪ ያሳውቃል፣
ቀ) የጉዳዮች ፍሰት አመራርና አስተዳደር ተግባራዊነት የሚጠበቅበትን ይሠራል፣
በ) በክፍሉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከባለጉዳዮች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል ምላሽ እንዲያገኙ ይሠራል፣
ተ) በፕሬዚዳንቱ፣ በምክትል ፕሬዝዳንትና ጉዳዩ በሚመለከተው አስተባባሪ የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፤
- የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር ተጠሪነቱ ለዋና ሬጅስትራር ሆኖ የሚከተሉትን ዝርዝር ተግባራት ያከናውናል፡-
ሀ) በፍትሐብሔርና በወንጀል የሥነ-ሥርዓት ሕግ እና በሌሎች ሕግጋት ለሬጅስትራር የተሰጡ ተግባራትን ያከናውናል፣
ለ) ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ አቤቱታዎች በስነ-ስርዓት ሕጎች የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልተው የተዘጋጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
ሐ) ለአከፋፈል እንዲያመች የተጠየቀውን ዳኝነት በመለየት ጉዳዩን ወደ ሚመለከተው ክፍል ያስተላልፋል፣ፋይሎች እንዲከፈቱ ይመራል፣
መ) የችሎት መዛግብት በቀጠሮ እንዲቀርቡ ያደርጋል፣
ሠ) በዳኛ የተሰጡ ትዕዛዞችን በማረጋገጥ ፈርሞ ወጪ ያደርጋል፣
ረ) በተንቀሳቃሽና በተዘጉ መዝገቦች ዙሪያ ለሚቀርቡ አግባብ ለሆኑ ጥያቄዎች መረጃዎችን ይሰጣል፣
ሰ) በዋና ሬጅስትራሩ የሚሰጡ የሥራ ክፍሉን ተጨማሪ ተግባራት ያከናውናል፣
ሸ) ዋና ሬጅስትራሩ በሌለ ጊዜ ተክቶ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
046-55-62-112




