
አቶ ሰለሞን መሽሻ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን እና ሚድያ ግንኙነት ዳሬክቶሬት
የጠቅላይ ፍ/ቤት የህዝብ ግንኙነት መሠረታዊ ዓላማዎች
- የጠቅላይ ፍ/ቤቱ የሚመራባቸዉን ህጎች የሚያስፈፅማቸዉን ደንቦችና መመሪያዎች የሚተልማቸዉ የልማት ዐቅዶችና አፈፃፀማቸዉን በየጊዜዉ ለህዘቡ ለተገልጋዩ በልዩ ልዩ መንገድ ማስተዋወቅ፡፡
- ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በሚሠጣቸዉ አገለረገረሎቶች ላይ የሚሰነዘሩ አስተያየቶችን ተከትሎ በማጥናትና በመገምገም በመልካም ጎን የቀረቡ ከሆነ ማሻሻያ የሚያገኝበትን መንገድ መጠቆም፡ ለአሉታዊና በአፍራሽነት ለቀረቡት ደግሞ የማስተባበያ ሀሳብ መስጠት
- የጠቅላይ ፍ/ቤት የበላይ ሀላፊዎችና ሌሎች የስራ ዘርፎች በኢንፎረሜሽን ኮሚኒኬሽን ዘርፍና በሚድያ አጠቃቀም ዙሪያ የማማከር አገልግሎት መስጠት፡፡
- ጠ/ፍ/ቤትን የሚመለከቱ ማንኛዉም አይነት መረጃዎችና ጥያቄ ስቀርቡለት ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ የስራ ክፍሎች መረጃዎችን አሰባስቦ በማጠናቀር ጠያቄዉን ላቀረቡት አካላት እንድደርሳቸዉ ማድረግ፡፡
- በአመራርና በሠራተኛዉ በሰራተኛዉ መካከል እንዲሁም በመላ ሰራተኛም ጤናማ የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲሰፍን የመ/ቤቱን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የጋራ ዓላማና ተግባር እንዲኖራቸዉ የማድረግ እንዲሁም በስራዉና በመ/ቤቱ ላይ የባለቤትነት ስሜት አሳድረዉ እርስ በርስ የሚተጋገዙበትና የሚተባበሩበት ሁኔታ ማመቻቸት፡፡
- ከሌሎች መ/ቤቶች ፡ተቋማት ፡ድርግቶችና ግለሰቦች ጋር የሚኖረዉ የሁለትዩሽ ግንኙነት እንዲሰምር የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠር በዉስጥ ያሉ ፕሮግራሞች ና ተቋማዊ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ እንዲታወቅና እነዲሰርፁ በማድረግ በአንድ በኩል የዜጎችን ግንዛቤ አሳድጎ ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ሊያስችል በሌላ በኩል ደግሞ የተቋሙን ምላሽ የመስጠት ብቃት ያረጋግጣል፡፡
046-55-62-112




