የጠቅላይ ፍ/ቤት የኋላ ታሪክ
በቀድሞ የደቡብብሄሮችብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የህግ ተርጓሚዉ የመንግስት አካል የነበረዉ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደነበረ ይታወቃል፡፡
በክልላችን ከተነሳዉ የህዝባዊጥያቄ ዉስጥ አንደኛዉ የፍትህ ተደራሽነት የመዋቅራዊ አደረጃጀት በመሆኑ በዚህ መነሻነት በ2012 ዓ.ም የሲዳማ ክልል በ2013 የደቡብ ምዕራብ ክልል ከነባሩ ክልል በመዉጣት በክልልነት መደራጀታቸዉ ይታወቃል፡፡የተቀረዉ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መ በነባሩ መዋቅሮች ይነሱ የነበሩ የአደረጃጀትና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት በ2015 ዓ.ም የደቡብ ክልል ለብቻዉ ክልልነትን መስርቷል፡፡ የተቀረዉ መዋቅርም የቀድሞዉን ህግን አደረጃጀት አሰራሮችን በማሻሻል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማለት የክልሉን ህገ-መንግስት በማፅደቅ በ2016 ዓ.ም ተደራጅቷል፡፡
ይህንን አደረጃጀትበመከተል በፌደራልም ሆነ በክልሉ ህገ-መንግስት የዳኝነት ስልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ እንደሆነ በተደነገገዉ መሠረት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የዜጎችን መብትና ነፃነት ለማስከበር የፍርድ ቤቶችን አዋጅ ቁጥር 1/2016 ዓ.ም እንዲሁም የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 2/2016 ዓ.ም በክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት አዋጁ ፀድቆ ተቋቁሟል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልጠቅላይ ፍርድ ቤት መቀመጫዉን ሀላባ ቁሊቶ ከተማ በማድረግ የዳኝነት አገልግሎት ስራዉን ከማንኛዉም ተፅዕኖ ነፃ በሆነ መንገድ ህግን በመተርጎም ክርክሮች ላይ እልባት በመስጠት በህገ- መንግስትና በህግ ብቻየሚመራ የዳኝነት አካል በመፍጠር በገለልተኝነት በህዝብ አገልጋይነት ስሜት በቅልጥፍና እና በሚዛናዊነት ለክልሉ ማህበረሰብ ጥራት ያለዉ የዳኝነት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
046-55-62-112




