Skip to main content

 

 

አቶ ኤርምያስ ኦልካሞ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰው ሀብት አስተዳደር ዳሬክቶሬት

 

 

   
 
 ስልክ ቁጥር 0465562112

የክልል ፍርድ ቤቶች የሰው ሀብት አስተዳደር

  1. የክልሉ ፍርድ ቤቶች የየራሳቸውን የአስተዳደር ሠራተኞች የመመልመል፤ የመቅጠር፤ የመመደብ እና የማስተዳደር ሙሉ ነጻነት አላቸው፤
  2. የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለዳኝነት ሥራ አስፈላጊ የሆኑ የአስተዳደር ሠራተኞችን የሥራ መደቦችን፤ ደረጃዎችን እና መመልመያ መስፈርቶችን በየደረጃው ላሉ ፍርድ ቤቶች የማዘጋጀት ሙሉ ነጻነት አለው፤
  3. የክልል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ምልመላ፣ ቅጥር፣ ምደባ፣ እድገት፣ዝውውር፣ ስልጠና፣ ደመወዝ፣ ጥቅማ ጥቅም፣ የዲሲፕሊን ጉዳይ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፤
  4. በንዑስ አንቀጽ (3) መሰረት የሚወጣው ደንብ የፍርድ ቤቶችን ልዩ የሥራ ጠባይ፣ እያንዳንዱ የስራ መደብ የሚጠይቀውን ተፈላጊ ችሎታና ልምድ፣ የሥራ ዝርዝሮችን ይዘትና ስፋትና ሌሎች ተዛማጅ መመዘኛዎችን ታሳቢ በማድረግ የሚወሰን ይሆናል፤
  5. የአስተዳደር ሠራተኞች መብት እና ጥቅማ ጥቅም በመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ለሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ከተፈቀደው ሊያንስ አይችልም፤

የአስተዳደር ሠራተኞችን በተመለከተ የሚወጡ ሕጎች እና የሚተላለፉ ውሳኔዎች ሁሉ ከፍርድ ቤቶች ተቋማዊ ነጻነት ጋር የተጣጣሙ መሆን አለባቸው፡፡

 

የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ተግባራት 

  • የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣  ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፣
  • ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
  • የተቋሙን ሠራተኞች መንግሥት በወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያከናውናል፣
  • በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና
  • የመንግስት መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ሰርኩላሮችና አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችን ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል፣
  • ሜሪቲን የተከተለ የሰው ሀብት ምልመላና መረጣ እንዲከናወን ያደርጋል፣
  • ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችና አገልግሎቶች ሳይዛቡ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
  • ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሃብት የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ እንዲከናወን ያደርጋል፣
  • የሠራተኛ የግል ማህደሮች ተሟልተውና ዘመናዊ ሆነው እንዲያዙ ክትትል ያደርጋል፣
  • አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
  • በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው  ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣
  • አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
  • የዳይሬክቶሬቱን  ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፣
  • የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ፣ እንዲደራጁ ተተንትነው እንዲጠናቀሩ ያደርጋል፣
  • የመረጃዎችን ትክክለኝነት ያረጋግጣል፣ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፣
  • በደረጃው ለተፈቀዱ የስራ መደቦች የሰው ኃይል ስምሪት ፈተናዎችን ያዘጋጃል፣ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችም እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ይፈትናል፣ እንዲፈተኑ ያደርጋል፣ ያርማል፣ እንዲታረሙ ያደርጋል፣ መረጃዎቹን በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ /በሃርድና በሶፍት ኮፒ/ ተደራጅተው እንዲያዙ ያደርጋል፣
  • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ መመሪያዎች እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የጥናት ውጤቶችን ይገመግማል፣
  • ለሥራ መደቦች የሥራ ትንተና ተከናውኖ የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣
  • ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሃብት የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ ጥናቶች እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የተጠኑትን ይገመግማል፣  ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ 
  • የሀገር ውስጥና የውጭ አገር ተሞክሮዎችን ይዳስሳል፣ ይቀምራል፣ እንዲቀመር ያደርጋል፣ ጠቃሚ የሆኑት በሥራ እንዲተረጎሙ ያደርጋል፣
  • መልካም ተሞክሮዎችን በማጣጣም ዳይሬክቶሬቱ የሚመራበትን አዳዲስ አሰራሮች በመቀመር እንዲቀመር በማድረግ፣ በመገምገም የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ ያስፋፋል፤
  • ለመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን መመሪያን ተግባራዊ ማድረግ 
  • በዲሲፕሊን እንዲታዩ በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ ተገቢና አስተማሪ እርምጃ መውሰድ
  • የሰራተኞችን የትምህርት መረጃ ማጣራት