Skip to main content

 

 አቶ አንዳርጋቸው ይድነቃቸው  

 የማ/ኢ/ጠ/ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት

 

 

 

 

 

 

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ተጠሪነቱ ለፕሬዚዳንቱ ሆኖ ፕሬዝዳንቱ በማይኖርበት ወይም ሥራውን ለማከናወን በማይችልበት ጊዜ እና ሁኔታ ተክቶ ይሠራል፤

በንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው አጠቃላይ መርሕ እንደተጠበቀ ሆኖ ምክትል ፕሬዚዳንት የሚከተሉት ዝርዝር ሥልጣንና ተግባራት አሉት፡-

ሀ) የዳኝነት አገልግሎት ዘርፉን የሥራ እንቅስቃሴ በቅርብ ይከታተላል፣ ተገቢውን ድጋፍ ይሰጣል፣ ጉድለት ባጋጠመ ጊዜም ከፕሬዚዳንቱ ጋር በመመካከር ተገቢውን የእርምት እና የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣

ለ) የጠቅላይ ፍርድ ቤት የአቤቱታ መስማትና መወሰን ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ፣ የምድብ ችሎት አስተባባሪዎችን፣ ችሎት ሰብሳቢ ዳኞችን፣ ሌሎች ዳኞችን እና የዳኝነት አስተዳደር ጉባዔ ተሿሚዎችን ስራ ያቀናጃል፣ያስተባብራል፣

ሐ) ከዳኝነት አገልግሎት ጋር ግንኙነት ያላቸውን የሕግ ረቂቆች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲጸድቁም አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣

መ) የዳኝነት አገልግሎትን ለማሻሻል የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደርን ይከታተላል፣

ሠ) በፕሬዚዳንቱ ተለይተው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡