Skip to main content
Image removed.
  1. የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር
  2. የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በሕግ መሰረት የክልሉን ፍርድ ቤቶች ለማስተዳደር   ሥልጣንና ኃላፊነት አለው፤
  3. በንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው አጠቃላይ መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሚከተሉት ዝርዝር ሥልጣንና ተግባራት አሉት፡-

ሀ) የክልሉን ፍርድ ቤቶች በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ ያስተዳድራል፣

ለ) የክልሉ ፍርድ ቤቶች ዓመታዊ ሪፖርት፣ የስራ ዕቅድ እና በጀት አዘጋጅቶ ለክልሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ እንዲጸድቅ ያደርጋል፣ በጀቱንም ያስተዳድራል፣ በሥራ ላይ ያውላል፣

ሐ) የፍርድ ቤቶች የአፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በየሩብ ዓመቱ ይልካል እንዲሁም በዓመት ሁለት ጊዜ ያቀርባል፣

መ) የዞን ወይም የልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች፣ የወረዳ ወይም የከተማ አስተዳደር  የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች  የተመደበላቸው በጀት ለሥራው በቂ መሆኑን ይከታተላል፣ የፀደቀላቸው በጀት ሥራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣

ሠ) የክልሉን የዳኝነት አገልግሎት ፖሊሲ እና ስልት ያዘጋጃል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣

ረ) ለሹመት በዕጩነት የሚቀርቡ ዳኞችን እና የዳኞች አስተዳደር ዋና ጉባዔ ተሿሚዎችን ለሚመለከታቸው አካላት ለሹመት ያቀርባል፣

ሰ) የጠቅላይ ፍርድ ቤት የችሎት ሰብሳቢ ዳኞችን ይመድባል፣ ዳኞችን በየችሎት ይደለድላል፤ዝርዝር የአፈፃፀም መስፈርቱ በመመሪያ ይወሰናል፡፡

ሸ) በየደረጃው ያሉ ዳኞች በመልካም ሥነ-ምግባር የታነጹ ስለመሆናቸው ይከታተላል፣ያረጋግጣል፣

ቀ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የቀረበለትን የመዋቅር ጥናት ተመልክቶ ይወስናል፣ አስፈላጊ የሆኑ የአስተዳደር ሠራተኞችን የሥራ መደብ እና ደረጃ ይወስናል፣ በዚሁ መሠረት ቅጥር እንዲፈጸም ያደርጋል፣

 

  1. የዋና ጉባዔ ሥልጣንና ተግባር

የክልሉ የዳኝነት አስተዳደር ዋና ጉባዔ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

  1. የክልሉ የዳኝነት አገልግሎት የሚሻሻልበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤
  2. የፍርድ ቤቶችና የዳኞች ነጻነትና ተጠያቂነት ሚዛናዊ እንዲሆን ይሰራል፤
  3. የዳኞች ብቃት፣ መልካም ጠባይና ሥነ-ምግባር የሚዳብርበትን ተግባር ያከናውናል፤
  4. የተገልጋዩ፣ የኅብረተሰቡና የመንግሥት እርካታና አመኔታ የሚጠናከርበትን ስልት በመንደፍ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ ድጋፍ ያደርጋል፤
  5. በክልሉ ፍርድ ቤቶች በዳኝነት ሙያ ለመሰማራት ብቁ ሆነው የተገኙ ዕጩ ዳኞችን ለክልሉ ምክር ቤት እንዲሾሙ አስተያየት ያቀርባል፤
  6. የጠቅላይና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት ለክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከማቅረቡ በፊት የፌዴራል የዳኞች አስተዳደር ጉባዔን አስተያየት ይጠይቃል፤
  7. የዞን ወይም የልዩ ወረዳ ወይም የወረዳ ወይም የከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት ለክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከማቅረቡ በፊት ከሚመለከተው የአስተዳደር ምክር ቤት አስተያየት ይጠይቃል፤
  8. የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን፣ የከፍተኛና የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞችን እንዲሁም የዳኞች አስተዳደር ዋና ጉባዔ ተሿሚዎችን የሥራ ቦታ ዝውውር ይወስናል፣ ዝርዝሩ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣው የአፈጻጸም መመሪያ ይወሰናል፤
  9. የዳኞችን፣ የዋና እና የንኡስ ጉባዔ ተሿሚዎችን፣የተከላካይ ጠበቆችን፣ የረዳት ዳኞችን ደመወዝ፣ አበል፣ እረፍት፣ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን፣ ሕክምና፤ ደረጃና የዕድገት መሰላል እንዲሁም የፕሬዚዳንቶችን እና ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ደመወዝና ጥቅማጥቅም አጥንቶ በማጸደቅ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ዝርዝሩ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣው የአፈፃፀም መመሪያ ይወሰናል፤
  10. የዳኞችንና የዳኝነት አስተዳደር ጉባዔ ተሿሚዎችን በተመለከተ መተዳደሪያ ደንብ ወይም የሥነ-ምግባርና የዲሲፕሊን ውስጠ-ደንብ በማውጣት በስራ ላይ ያውላል፤
  11. የዳኞችን፣ የዋና እና የንኡስ ጉባዔ ተሿሚዎችን የሥራ አፈጻጸም መመዘኛ ሥርዓት በመዘርጋት ተግባራዊ ያደርጋል፤
  12. በክልሉ ፍርድ ቤቶች ዳኞች፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶችና ምክትልፕሬዚዳንቶች እንዲሁም በዋናም ሆነ በንኡስ ጉባዔ ተሿሚዎች ላይ የሚቀርቡ የሥነ ምግባርና የዲሲፕሊን ጥሰት ክሶችን፣ ጉልህ የሥራ ችሎታና ቅልጥፍና ማነስ ጉዳይን እና በህመም ምክንያት ሥራን ማከናወን አለመቻል ሁኔታን የሚቀርብለት ይግባኝ ተመልክቶ ውሳኔ ይሰጣል፤
  13. ጉልህ የሥራ ችሎታና ቅልጥፍና ማነስ የታየባቸው፣ በሕመም ምክንያት ሥራቸውን ማከናወን ያልቻሉ ዳኞችን እና የዳኝነት አስተዳደር ጉባዔ ተሿሚዎችን በሚመጥናቸው ሥራ ይመድባል፣ ስለሚከፈላቸው የደመወዝ መጠንም ይወስናል፣ ወይም እንደነገሩ ሁኔታ ከሥራ ያሰናብታል፤
  14. በንዑስ ጉባዔ ታይቶ ከሥራ እንዲሰናበት የውሳኔ ሀሳብ የቀረበበትን ዳኛ ወይም ቃዲ ጉዳይ መርምሮ ተገቢውን ይወስናል፤
  15. በወንጀል ጉዳይ የተጠረጠረን ዳኛ በተመለከተ የቀረበለትን ጥያቄ አሳማኝ ሆኖ ካገኘው የዳኛውን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ያደርጋል፤
  16. በዋና ጉባዔ ጽህፈት ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበለትን ረቂቅ ዓመታዊ የስራ ዕቅድ መርምሮ ያጸድቃል፣ አፈጻጸሙንም ይገመግማል፤ 
  17. የዋና እና ንኡስ ጉባዔ ጽህፈት ቤቶች የስራ አፈጻጸም መመሪያ በማውጣት ተፈጻሚ ያደርጋል፤
  18. የዋና ጉባዔም ሆነ የንዑስ ጉባዔ አባላት በሚሰበሰቡበት እና ለሥራ በሚሰማሩበት ጊዜ ሊከፈላቸው የሚገባውን የአበል መጠን ይወስናል፤
  19. አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በወረዳ ፍርድ ቤት ደረጃ የሥነ-ምግባር ክትትል እና ኢንስፔክሽን ባለሙያ እንዲመደብ ደረጃውን ለይቶ ይወስናል፤
  20. ክስ የቀረበበት ዳኛ ወይም የዳኝነት አስተዳደር ጉባዔ ተሿሚ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በሥራ ላይ ቢቆይ በደል ያደርሳል ብሎ ያመነ እንደሆነ ደመወዙ እየተከፈለው ለጊዜው ከሥራ ታግዶ እንዲቆይ ሊያደርግ ይችላል፤
  21. በማንኛውም ምክንያት አንድ ዳኛ ከሥራ እንዲሰናበት ጉባዔው በወሰነ ጊዜ ዳኛውን ከሥራ በማገድ ለመጨረሻ ውሳኔ ለክልሉ ምክር ቤት ያቀርባል፤
  22. የዲሲፕሊን ክስ በቀረበለት ጊዜ የተከራካሪ ወገኖችን እኩል የመሰማት መብት ያረጋግጣል፤
  23. በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቅራቢነት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት፣ የዋና እና የክልል ንኡስ ጉባዔ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ የክልሉን የተከላካይ ጠበቆች ጽህፈት ቤት ኃላፊን እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረጃ የሚሰሩ ተከላካይ ጠበቆችን፣በጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረጃ የሚሰሩ የአቤቱታ መስማትና መወሰን ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪዎችን፣ የምድብ ችሎት አስተባባሪዎችን፣ በየደረጃው የሚገኙ የሸሪአ ፍርድ ቤት ቃዲዎችንና ሌሎች የጉባዔ ተሿሚዎችን ይሾማል፣ እንዳስፈላጊነቱም ከኃላፊነት ያነሳል፤
  24. ሌሎች ተዛማጅ የሆኑና በሌሎች ህጎች የተሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፡፡

 

 

  1. የክልል ንኡስ ጉባኤ ሥልጣንና ተግባር

የክልል ንኡስ ጉባኤ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

  1. በጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረጃ ያሉ የጉባኤ ተሿሚዎች፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች ላይ የሚቀርቡ የሥነ-ምግባር ጥሰት ክስን አይቶ ይወስናል፤
  2. የሥነ-ምግባር ጉዳይን አስመልክቶ በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ተጨማሪ ሥራ ይሰራል፡፡
  3.  የክልል ንኡስ ጉባኤ ሰብሳቢ ሥልጣንና ተግባር

የክልል ንኡስ ጉባኤ ሰብሳቢ ተጠሪነት ለፕሬዝዳንቱ ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡-

  1. የንኡስ ጉባኤውን ስብሰባ ይጠራል፣ ይመራል፤
  2. የሥነ-ምግባር ጉዳዮችን ተቀብሎ ለንኡስ ጉባኤው ያቀርባል፤
  3. የንኡስ ጉባኤውን ሥራ አደራጅቶ ይይዛል፣ የሥነ-ምግባር መረጃን ያጠናክራል፣ ይይዛል፤
  4. የንኡስ ጉባኤውን መዛግብትንና ሰነድ በአግባቡና በዘመነ መልኩ መያዛቸውን ያረጋግጣል፤
  5. የንኡስ ጉባኤውን ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ ዋና ጉባኤ ጽህፈት ቤት ያቀርባል፤
  6. በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

 

 

በ) የፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ወጪ ቆጣቢ፣ ተደራሽ፣ ተገማች እና ለህዝብ ግልጽ የሚሆንበትን የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ ውጤታማ ለማድረግ የሚረዳ አዳዲስ የአሠራር ሥልቶችን እንዲቀየሱ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣

ተ) የዳኝነት ሥራን ለማጠናከር እና ለማሻሻል ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት ይሠራል፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር መልካም ተሞክሮዎችን ይዳስሳል፣ የክልል ዳኞች የተሻለ ልምድ የሚቀስሙበትን እና በየጊዜው ራሳቸውን በዕውቀት፣ በክህሎት እና በአመለካከት የሚገነቡበትን ስልት በማጥናት ተግባራዊ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፣

ቸ) በክልል ውስጥ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ድጋፍ ያደርጋል፣

ነ) ዳኞች፣ የጉባኤ ተሿሚዎች እና የሌሎች የአስተዳደር ሠራተኞች ትምህርትና ሥልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣

ኘ) የዳኝነት ሥራ ለማጠናከር የሚረዱ የምርምር ሥራዎች እንዲደረጉ እና የዓመቱ ፍርዶች፣ ውሣኔዎች ተመርጠው በሕግ መጽሄት  እንዲታተሙ ያደርጋል፣

አ) ለፍርድ ቤቶቹ ሥራ የበለጠ መሻሻልና በአጠቃላይ ፍርድ ቤቶች ለኅብረተሰቡ የሚሰጡትን የፍትሕ አገልግሎት ለማጠናከር አስፈላጊ የሆኑ የሕግ ረቂቆች በህግ ስልጣን ከተሰጠው አካል ጋር በመተባበር እንዲዘጋጁ እና ለክልል ምክር ቤት ቀርበው እንዲጸድቁ ያደርጋል፣ ተፈጻሚነታቸውንም ይከታተላል፣

ኸ) የክልሉ ፍርድ ቤቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣን የዳኝነት አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፣

ወ) በክልል ፍርድ ቤቶች ፕሮግራሞችና የሥራ ዕቅዶች ውስጥ የሥርዓተ ጾታ ጉዳዮች ስለመካተታቸው ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣

ዘ) ከሶስተኛ ወገን ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ይወክላል፣

ዠ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ጉዳይ በውክልና ለሚሠሩ ፍርድ ቤቶች ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የበጀት ማካካሻ ይጠይቃል፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣

የ) በዚህ አዋጅ እና በሌሎች  ሕጎች የተሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

 

 

  1. የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር
  2. የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ተጠሪነቱ ለፕሬዚዳንቱ ሆኖ ፕሬዝዳንቱ በማይኖርበት ወይም ሥራውን ለማከናወን በማይችልበት ጊዜ እና ሁኔታ ተክቶ ይሠራል፤
  3. በንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው አጠቃላይ መርሕ እንደተጠበቀ ሆኖ ምክትል ፕሬዚዳንት የሚከተሉት ዝርዝር ሥልጣንና ተግባራት አሉት፡-

ሀ) የዳኝነት አገልግሎት ዘርፉን የሥራ እንቅስቃሴ በቅርብ ይከታተላል፣ ተገቢውን ድጋፍ ይሰጣል፣ ጉድለት ባጋጠመ ጊዜም ከፕሬዚዳንቱ ጋር በመመካከር ተገቢውን የእርምት እና የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣

ለ) የጠቅላይ ፍርድ ቤት የአቤቱታ መስማትና መወሰን ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ፣ የምድብ ችሎት አስተባባሪዎችን፣ ችሎት ሰብሳቢ ዳኞችን፣ ሌሎች ዳኞችን እና የዳኝነት አስተዳደር ጉባዔ ተሿሚዎችን ስራ ያቀናጃል፣ያስተባብራል፣

ሐ) ከዳኝነት አገልግሎት ጋር ግንኙነት ያላቸውን የሕግ ረቂቆች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲጸድቁም አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣

መ) የዳኝነት አገልግሎትን ለማሻሻል የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደርን ይከታተላል፣

ሠ) በፕሬዚዳንቱ ተለይተው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የክልል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር

  1. የዳኝነት ነጻነት
  2. በየትኛውም እርከን የሚገኝ የክልል ፍርድ ቤት ወይም ዳኛ ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ባለሥልጣን ወይም ሌላ አካል ተፅዕኖና ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆኖ ሥራውን በሕግ መሰረት ያከናውናል፤
  3. ዳኞች ስራቸውን ከማንኛውም የውስጥና የውጭ ተጽዕኖ ነጻ ሆነው በማከናወን በሕግና ፍሬ-ነገር ላይ የተመሰረተ ፍርድ፣ ብይን፣ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ይሰጣሉ፤
  4. ማንኛውም የመንግሥት አካል፣ የመንግሥት ባለሥልጣንም ሆነ ሌላ ማንኛውም ሰው የክልሉን ፍርድ ቤቶች ተቋማዊና የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነት የማክበር ግዴታ አለበት፤
  5. ማንኛውም የመንግሥት አካል፣ የመንግሥት ባለሥልጣንም ሆነ ሌላ ማንኛውም ሰው በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ፣ ውሳኔ፣ ብይን ወይም ትዕዛዝ የማክበርና የመፈጸም ግዴታ አለበት፤
  6. የክልሉ ፍርድ ቤቶች በበጀት፣ በሰው ኃይል አስተዳደር እና በውስጥ አሰራራቸው  እራሳቸውን ችለው ይሠራሉ፡፡
  7. የዳኝነት ተጠያቂነት
  8. በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የክልል ፍርድ ቤት ከተሰጠው ኃላፊነት አንጻር በሕግ መሠረት ተጠያቂነት አለበት፤
  9. ዳኞች የያዙት ክርክር ሂደት ተከራካሪ ወገኖችን ያለአድሎዎ በእኩልነት የሚያስተናግዱ መሆኑን የማረጋገጥ ግዴት ይኖርባቸዋል፤ በተለይም በወንጀል የተከሰሱ ወይም በጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎችን አያያዝ ሁኔታ የመከታተል፤ ሰብአዊ መብቶቻቸውን የማክበር እና የማስከበር የእነዚህ መብቶችን ጥሰት የሚመለከት አቤቱታ በቀረበ ጊዜም ጉዳዩ አግባብ ባለው አካል ተጠርቶ ተገቢው እንዲፈፀም ትዕዛዝ የመስጠት ሃላፊነት አለባቸው፡፡
  10. በሌሎች ሕጎች የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ዳኛ የዲሲፕሊንና የሥነምግባር ጥፋት ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ በዳኝነት አስተዳደር ዋና ጉባዔ የዲሲፕሊን ደንብ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

 

 

  1.  የፍርድ ቤቶች በጀትና የበጀት አስተዳደር
  2. የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሥራው የሚያስፈልገውን ጥቅል በጀት በማዘጋጀት በቀጥታ ለክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል፣ የጸደቀለትንም በጀት ያስተዳድራል፤
  3. የዞን ወይም የልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሥሩ ያሉ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ ለሥራ የሚያስፈልገውን ጥቅል በጀት በማዘጋጀት በቀጥታ ለዞን ወይም ለልዩ ወረዳ ምክር ቤት በማቅረብ ያስወስናል፣ የጸደቀለትንም በጀት ያስተዳድራል፤
  4. ለክልል የዳኝነት አካል የሚመደበው በጀት ፍርድ ቤቶች የተሰጣቸውን ሥልጣን እና ኃላፊነት በተሟላ ሁኔታ ለማከናወን የሚያስችል መሆን አለበት፡፡
  5. የክልል፣ የዞን ወይም ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ለዳኝነት አካል ጥቅል በጀት ሲመድቡ የፍርድ ቤቶችን የሥራ ስፋት፣ መሰረታዊ ፍላጎት ያገናዘበ በጀት ሊመደብ ይገባል፡፡
  6. የክልል ፋይናንስ ቢሮ ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በምክር ቤቱ የጸደቀውን ጥቅል በጀት የፋይናንስ አሠራርን ተከትሎ በሚያቀርበው መጠየቂያ መሠረት በየሩብ ዓመቱ መጀመሪያ ሳምንት ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የባንክ ሒሳብ ማስገባት አለበት፤
  7. የዞን ፋይናንስ መምሪያ፤ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳ ወይም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ለዞን፤ ለልዩ ወረዳ፣ ወረዳ ወይም ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት የጸደቀውን ጥቅል በጀት የፋይናንስ አሠራርን ተከትሎ በሚቀርበው መጠየቂያ መሠረት በየሩብ ዓመቱ መጀመሪያ ሳምንት በየፍርድ ቤቱ ባንክ ሒሳብ ማስገባት አለበት፤
  8. የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የበጀት አጠቃቀም በተመለከተ ለክልል የሕዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት ሪፖርት የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፤
  9. የዞን፤ ልዩ ወረዳ፤ ወረዳ ወይም ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የበጀት አጠቃቀም በተመለከተ ለየምክር ቤቶቻቸው ሪፖርት የማቅረብ ኃላፊነት አለባቸው፤
  10. የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በውክልና ከሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የበጀት ማካካሻ ጥያቄ የማቅረብ መብት አለው፡፡

 

 

 

  1. የአቤቱታ መስማት እና መወሰን የሥራ ሂደት አስተባባሪ ሥልጣንና ተግባር 

አቤቱታ መስማት እና መወሰን የሥራ ሂደት አስተባባሪ ተጠሪነቱ ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚከተለው ዝርዝር ሥልጣንና ተግባራት አሉት፡-

  1. የሥራ ሂደቱን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤
  2. ተጠሪ ለሆነለት አካል የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤
  3. ለስራ ሂደቱ የሚመደብለትን ዓመታዊ በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ያደርጋል፤
  4. በጉዳዮች መለኪያ ወይም ስታንዳርድ መሠረት በሥሩ ለሚገኝ የሥራ ክፍል የሥራ ስምሪት ይሰጣል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  5.  የሥራ ሂደቱን ሥራዎች በበላይነት ያስተባብራል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
  6.  ጠንካራና ደካማ አፈፃፀሞችን በመለየት ችግር ፈቺ በሆኑ ሀሳቦች ላይ የስራ ሂደቱን አባላት ያወያያል፣ መፍትሔ ይሰጣል፤
  7.  የመዝገቦችን ብዛት እና የጉዳዮችን ፍሰት እያጠና የተሻለ የአሠራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ለምክትል ፕሬዝዳንቱ ሃሳብ ያቀርባል፤
  8.  በሥሩ በሚገኙ ችሎቶች የሚያስችሉ ዳኞች ተሟልተው ማስቻላቸውንና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን ይከታተላል ፣ይቆጣጠራል፣ ጉድለት በታየ ጊዜም ከምክትል ፕሬዝዳንቱ ጋር በመመካከር ተገቢውን ማስተካከያ ያደርጋል፤
  9.  ከመዛግብት ጋር በተያያዘና የስራ ሂደቱን በሚመለከት በባለጉዳዮች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይቀበላል፣ መፍትሔ ይሰጣል፤
  10. የስራ ሂደቱን አባላት የሥነ-ምግባር ሁኔታ ይከታተላል፣ የሚታዩ ጉድለቶችንም በመለየት የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣ እንደአጥፊው ማንነት ለንኡስ ጉባዔ ጽህፈት ቤት ወይም ለአስተዳደር ሠራተኞች የሰው ሐብት አስተዳደር ያቀርባል፤
  11. በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፤
  12. በዞን፤ ልዩ ወረዳ፤ በወረዳ  ወይም የከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የአቤቱታ መስማት እና መወሰን የሥራ ሂደት አስተባባሪ ተጠሪነት ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ሆኖ እንደአግባብነቱ በዚህ አንቀጽ የተዘረዘሩ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
  13. ዋና ሬጅስትራር እና የሬጅስትራር ሥልጣን እና ተግባር
  14. ዋና ሬጅስትራር ተጠሪነቱ እንደአግባቡ ለሚመለከተው የአቤቱታ መስማትና መወሰን የሥራ ሂደት አስተባባሪ ወይም ለምድብ ችሎት አስተባባሪ ሆኖ በሌላ ሕግ ከተደነገገው በተጨማሪ የሚከተሉት  ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

ሀ) የክፍሉን ሥራ በማቀድ ይመራል፣ያደራጃል፣ የማስተባበርና የቁጥጥር ስራን በመስራት ያስተዳድራል፣

ለ) የስራ ድጋፍና ግምገማ፣ የውጤት ምዘና ያካሄዳል፣ ለክፍሉ ስራ አስፈላጊ የሆነ አቅርቦት እንዲሟላ ያደርጋል፣ የእቅድ አፈፃፀም የስራ ሪፖርት ያቀርባል፣

ሐ) የችሎት አስተዳደር ሥራዎች በየዕለቱ መከናወናቸውን ይከታተላል፣ የአሠራር ክፍተት ሲኖር ለሚመለከተው  አስተባባሪ ያሳውቃል፣

መ) ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የችሎት አስተዳደር ሥራ እንዲኖር ከሚመለከተው አስተባባሪ ጋር በመነጋገር የተሻለ የአሠራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣

ሠ) ጉዳዩ ከሚመለከተው አስተባባሪ ጋር በመመካከር የቀጠሮ ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲሆን ይሠራል፣

ረ) በሚመለከተው የአቤቱታ መስማት እና መወሰን የሥራ ሂደት ወይም በምድብ ችሎት ለሚገኙ የሬጅስትራር ቡድን መሪዎች የሥራ ስምሪት ይሰጣል፣ ኃላፊነታቸውን በሚገባ ስለመወጣታቸው ይከታተላል፣ ጉድለት ሲኖር ከሚመለከተው አስተባባሪ ጋር በመመካከር ተገቢውን የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣

ሰ) በስሩ በሚገኙ ሬጅስትራሮችና የሬጅስትራር ቡድን መሪዎች ወይም ሰራተኞች የሥነ-ምግባር ጉድለት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከተው አስተባባሪ ያቀርባል፣

ሸ) ለሥራው የሚያስፈልጉ የሬጅስትራር ሠራተኞች እንዲሟሉ ለሚመለከተው አስተባባሪ ያሳውቃል፣

ቀ) የጉዳዮች ፍሰት አመራርና አስተዳደር ተግባራዊነት የሚጠበቅበትን ይሠራል፣

በ) በክፍሉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከባለጉዳዮች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል ምላሽ እንዲያገኙ ይሠራል፣

ተ) በፕሬዚዳንቱ፣ በምክትል ፕሬዝዳንትና ጉዳዩ በሚመለከተው አስተባባሪ የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፤

  1. የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር ተጠሪነቱ ለዋና ሬጅስትራር ሆኖ የሚከተሉትን ዝርዝር ተግባራት ያከናውናል፡-

ሀ) በፍትሐብሔርና በወንጀል የሥነ-ሥርዓት ሕግ እና በሌሎች ሕግጋት ለሬጅስትራር የተሰጡ ተግባራትን ያከናውናል፣

ለ) ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ አቤቱታዎች በስነ-ስርዓት ሕጎች የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልተው የተዘጋጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣

ሐ) ለአከፋፈል እንዲያመች የተጠየቀውን ዳኝነት በመለየት ጉዳዩን ወደ ሚመለከተው ክፍል ያስተላልፋል፣ፋይሎች እንዲከፈቱ ይመራል፣

መ) የችሎት መዛግብት በቀጠሮ እንዲቀርቡ ያደርጋል፣

ሠ) በዳኛ የተሰጡ ትዕዛዞችን በማረጋገጥ ፈርሞ ወጪ ያደርጋል፣

ረ) በተንቀሳቃሽና በተዘጉ መዝገቦች ዙሪያ ለሚቀርቡ አግባብ ለሆኑ ጥያቄዎች መረጃዎችን ይሰጣል፣

ሰ) በዋና ሬጅስትራሩ የሚሰጡ የሥራ ክፍሉን ተጨማሪ ተግባራት ያከናውናል፣

ሸ) ዋና ሬጅስትራሩ በሌለ ጊዜ ተክቶ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

 

  1. የተከላካይ ጠበቃ ሥልጣን እና ተግባር

ተከላካይ ጠበቃ ተጠሪነቱ በየደረጃው ላሉት ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡-

  1. በከባድ ወንጀል ተከሰው የራሳቸውን ጠበቃ አቁመው የመከራከር አቅም ለሌላቸው ሰዎች ወይም በማናቸውም የወንጀል ጉዳይ ፍትህ ይጓደላል ተብሎ ሲታመን ተከሳሽን ይወክላል፤
  2. የሕግ ምክር አገልግሎት ይሰጣል፣ መልስ፣አቤቱታዎችን፣ የይግባኝና የሰበር ቅሬታዎችን ያዘጋጃል፣ ክርክሮችን ያደርጋል፤
  3. በማረሚያ ቤት በመገኘት ጥብቅና የቆመለትን ተከሳሽ ወይም ታራሚ ያማክራል፤
  4. በመከላከያነት የሚያገለግል ደጋፊ ማስረጃ ያሰባስባል፣ያደራጃል፤
  5. የተከላካይ ጠበቆች ዝርዝር ተግባራት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡

 

  1. የጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ሥልጣንና ተግባራት

የአስተዳደር እና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ተጠሪነቱ ለፕሬዚዳንቱ ሆኖ የሚከተሉት ዝርዝር ሥልጣን እና ተግባራት ይኖሩታል፡-

ሀ) የክልል ፍርድ ቤቶች አስተዳደራዊ መዋቅር ተጠንቶ እንዲጸድቅ ያደርጋል፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በመመካከር የአስተዳደር ሠራተኞችን ቅጥር ይፈጽማል፣ ይመድባል፣ ያስተዳድራል፣

ለ) የአስተዳደር ዘርፉን የሥራ ሂደቶች እንቅስቃሴና ውጤታማነት በቅርብ ይከታተላል፣ ተገቢውን ድጋፍ ይሰጣል፣

ሐ) የአስተዳደር ሠራተኞችን የትምህርት እና የስልጠና ሁኔታ ያመቻቻል፣

መ) ከበጀት፣ ከመሠረተ ልማትና ሌሎች ሀብቶች እንዲሁም ከሰው ሀብት ጋር ግንኙነት ያላቸውንና በአጠቃላይ ዘርፉንና በዘርፉ ውስጥ ያለውን የአስተዳደር ሠራተኛ የሚመለከቱ ጥናቶች በማድረግ የውሳኔ ሐሳቦችንና ረቂቅ ሕጎችን እንዲዘጋጁ በማድረግ ለፕሬዚዳንቱ ያቀርባል፣ በሚመለከተው አካል ሲጸድቁ ተግባራዊ ያደርጋል፣

ሠ) የዘርፉን አሰራር ለመለወጥ ስልቶችን ይቀይሳል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፣ ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፣ ጉድለት ባጋጠመ ጊዜ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በመመካከር የእርምት እና የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣

ረ) በፕሬዚዳንቱ ተለይተው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

 

  1. የክልል ፍርድ ቤቶች የሰው ሀብት አስተዳደር
  2. የክልሉ ፍርድ ቤቶች የየራሳቸውን የአስተዳደር ሠራተኞች የመመልመል፤ የመቅጠር፤ የመመደብ እና የማስተዳደር ሙሉ ነጻነት አላቸው፤
  3. የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለዳኝነት ሥራ አስፈላጊ የሆኑ የአስተዳደር ሠራተኞችን የሥራ መደቦችን፤ ደረጃዎችን እና መመልመያ መስፈርቶችን በየደረጃው ላሉ ፍርድ ቤቶች የማዘጋጀት ሙሉ ነጻነት አለው፤
  4. የክልል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ምልመላ፣ ቅጥር፣ ምደባ፣ እድገት፣ዝውውር፣ ስልጠና፣ ደመወዝ፣ ጥቅማ ጥቅም፣ የዲሲፕሊን ጉዳይ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፤
  5. በንዑስ አንቀጽ (3) መሰረት የሚወጣው ደንብ የፍርድ ቤቶችን ልዩ የሥራ ጠባይ፣ እያንዳንዱ የስራ መደብ የሚጠይቀውን ተፈላጊ ችሎታና ልምድ፣ የሥራ ዝርዝሮችን ይዘትና ስፋትና ሌሎች ተዛማጅ መመዘኛዎችን ታሳቢ በማድረግ የሚወሰን ይሆናል፤
  6. የአስተዳደር ሠራተኞች መብት እና ጥቅማ ጥቅም በመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ለሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ከተፈቀደው ሊያንስ አይችልም፤
  7. የአስተዳደር ሠራተኞችን በተመለከተ የሚወጡ ሕጎች እና የሚተላለፉ ውሳኔዎች ሁሉ ከፍርድ ቤቶች ተቋማዊ ነጻነት ጋር የተጣጣሙ መሆን አለባቸው፡፡
  8.  ኦዲት

የክልል ፍርድ ቤቶች የሒሳብ መዝገብ እና የበጀት አጠቃቀም በክልል ዋና ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራል፡