Skip to main content

የማዕከላዊ አትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዞንና ከልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቶች ጋር የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ

=====

ጥር 8/2016 የማዕከላዊ አትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዞንና ከልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቶች ጋር የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደዋል።

ውይይት መድረኩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቶ ፕሬዝዳንት ኤርሲኖ አቡሬ እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ትክክል ጣሰው ጋር በመሆን መርተዋል።

የህዝብ እና የመንግስት አመኔታ እየቀነሰ መምጣቱን የተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች በማመላከታቸው ምክንያት በፍርድ ቤቶች አካባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የፍርድ ቤቶች የሪፎርም ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል። የፍርድ ስርዓቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ እርካታ የሚያገኝበት የፍትህ ስርዓት አገልግሎት መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል። ፍርድ ቤቶች በክርክር በቀረበላቸው ጉዳዮች ላይ አፋጣኝ ጥራት ያለው ምላሽ ለመስጠትና የሚያስችልና ማህበረሰቡ በቅርቡ አገልግሎት ሊያስገኙ የሚችል ፍኖተ ካርታ እንደሆነ አቶ ኤርሲኖ አቡሬ አንስተዋል።በፍርድ ቤቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ በተወሰኑ ሰዎች የስነ ምግባር ችግር ምክንያት ቅሬታዎች ይቀርባሉ ያሉት ፕሬዝዳንቱ ይህን የሚታገሉ ምስጉን አመራሮችና ባለሙያዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

አገልግሎት አሰጣጥጋር ተያይዞም ዜጎችን በተቀላጠፈ መልኩ ለማስተናገድ እንዲቻል ዘመናዊ አሰራሮችን ያማከሉ የህግ ማዕቀፎችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ተግበራዊ ማድረግ አለበት ብለዋል።

ህግ ማሻሻያ ስራዎች፣ውጤታማ አገልግሎት አሰጣጥ፤ ተጠያቂነት፣ ግልፅነት፣ የዳኝነት አገልግሎት ጥራት ማረጋገጥ፣ ቅልጥፍናና ውጤታማነት፣ የላቀ እና ውጤታማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግ፣ የወንጀልና የፍትሐብሔር ውጤታማ ፍትህ ስርአት መዘርጋት፣ የዳኝነት ተቋሙን አደረጃጀት ማስተካከልና እንደሚገባ አሳስበዋል።ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም ይህ ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ታችኛው መወቅር በዞንና ወረዳዎች እንደሚወርድ ገልጸዋል።ለፍርድ ቤቶች የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ሥራ መነሻ መሆናቸውን ገልፀው የህዝብ አመኔታ ያተረፈ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ፍትሀዊ የዳኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም መገንባት ከሪፎርሙ ትግበራ በኋላ የሚጠበቅ መሆኑን አብራርተዋል።የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ትክክል ጣሰው ህብረተሰቡ የፍትህ ስርዓቱ አመኔታን የሚጥልበት ማድረግ በፍኖተ ካርታ ላይ ውጤታማነት በተገቢው መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

አገልግሎት አሰጣጣችን በማሳደግ ዜጎች ፍትህን በተገቢው እንዲያገኙና በተቋማት ላይ ያላቸው እምነትና ቅብልነት ማሳደግ እንደሚጠበቅ አንስተዋል።ፍርድ ቤቶች ታማኝነትን ሊኖራቸውና ተገልጋዩ ማህበረሰቡ በፍርድ ቤቶች ላይ ያለው ከፍ ብሎ መታየት የሚያስችሉ የክልላዊ ሁኔታችን ያገናዘቡ ተግባራት መፈፀም እንደሚገባ አሳስበዋል።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2016 የመጀመሪያ ግማሽ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።በመጨረሻም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2016 በጀት አመት ዕቅድ እና የግብ ስምምነት ከዞኖችና ከልዩ ወረዳዎች ጋር ተፈራርመዋል።

Image
photo