ታህሳስ 07/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ደንብ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ተካሂዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ እንደተናገሩት የዳኝነት አገልግሎት ክፊያ ረጅም ዓመታትን በማስቆጠሩ መሻሻል እንደሚገባው ገልፀዋል።
በሀገር ደረጃ በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች የተደረገ በመሆኑ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያን ማሻሻል ተገቢና ተገልጋዩ ህብረተሰብ ለሚሰጠው አገልግሎት ተመጣጣኝ ክፊያ መክፈል ያስፈልጋል ብለው ፈጥኖ ወደ ተግባር እንዲገባም አሳስበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርስኖ አቡሬ የዳኝነት አገልግሎት ክፊያ ደንብ ከወጣው ከ60 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል ብለዋል።
በህብረተሰቡ ዘንድ ከሚታየው ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች አንፃር ደንቡን ማሻሻል ተገቢ ነው ብለዋል።
የክልሉ ፍርድ ቤትም በፍርድ ቤቶች ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ላይ ከተዘረዘረው የለውጥ ስራዎች ህጎችን ማሻሻል አንዱ በመሆኑ ቀደም ሲል ሁለት አዋጆችና አንድ ደንብ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ የማጽደቅ እና መመሪያዎችን በማውጣት ስራ ላይ እንዲውል መደረጉንም ገልፀዋል።
የዳኝነት አገልግሎት ክፊያ ረቂቅ ደንብ ፀድቆ ስራ ላይ ሲገባ የክልሉን የገቢ አቅም የሚጨምር በመሆኑ ከክልሉ ገቢዎች ቢሮ ጋር በቅንጅት መስራታቸውን ተናግረዋል።
የዳኝነት አገልግሎት ክፊያ ረቂቅ ደንብ መመሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
የምክክሩ ተሳታፊዎች በቀረበው የዳኝነት አገልግሎት ክፍያን ማሻሻልን በተመለከተ በታሪፉ ምጣኔ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል።
አዋጁ ባለጉዳዮች ፍርድ ቤት የማያስቀርቡ ጉዳዮችን ይዘው እንዳይቀርቡ የሚያደርግ ነው ብለው በትግበራ ወቅት ክፍተት እንዳይፈጠር በተገልጋዩ ህብረተሰብ ዘንድ የግዛቤ ስራዎች በደንብ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ከተሳታፊዎች ለተነሱት አስተያየት እና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በመድረኩ የቢሮ ኃላፊዎች፣ የዞንና ልዩ ወረዳዎች የፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
046-55-62-112




