Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 ዓ/ም የፍርድ ቤቶችን ስራ የመጀመሪያውን ሩብ አመት ድጋፍና ክትትል ግምገማ ለማድረግ የማኔጅመንት አባላት ተንቀሳቅሰዋል።

ህዳር 16/2017 ዓ/ም ለክትትልና ድጋፍ ቡድን አባላት መመሪያና ስምሪት የሰጡት የጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ ኤርሲኖ አቡሬ ድጋፍና ክትትል ከሚደረግባቸው ዋና ጉዳይ መካከል :-የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተከብሮ የልማቱና የዕድገቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የፍርድ ቤቶች ሚና ከፍተኛ ነው።

ስለዚህ የክልላችን ፍርድ ቤቶች በሚሰጧቸው የዳኝነት አገልግሎቶች ህግንና ህግን ብቻ አክብረው ስለማስከበራቸወ:፤

ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን በማሳደግ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነትና ተዓማኒነት እንዲኖረው የሚያስችል የዕቅድ ዝግጅት ምዕራፉን ማየት፣መገምገም ተገቢ ይሆናል።

ይህን ሩብ ዓመት አፈጻጸም በማየትም ለሚቀጥለው ቀሪ የስራ ጊዜ ዝግጅት በማድረግና ፍርድ ቤቶችን በማብቃትና በማወዳደር የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን የመሸለም የማበረታታት ስራ ለመስራት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባናል ብለዋል።

Image
photo