Skip to main content

በክልሉ የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት ሰብዓዊ መብታቸዉን ለመጠበቅ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ።

****

ህዳር 7/2018 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ጉዳይ አያያዝ አስመልክቶ ለሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዱራሜ አካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርስኖ አቡሬ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው ህፃናት በአካልና በአይምሮ የዳበሩ ባለመሆናቸዉ ልዩ ትኩረት አና አንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸዉ ገልጸዋል።የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ሰበአዊ መብታቸዉን ለማስከበር ፍርድ ቤቶች በልዩ ትኩረትና ጥበቃ ተሰጥቶባቸው እየተሰራ ስለመሆኑም ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።የህፃናት መብት ሰጣስና በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ለመከላከል ዳኞች በልዩ ትኩረት መስራት አለባቸዉ ብለዋል።

የህፃናት ጉዳይ ወንጀል ፈጽመዉ ሲገኙም ሆነ ወንጀል ስፈፀምባቸዉ ጉዳያቸዉ ከአዋቂዎች በተለየ ቦታና ሁኔታ መታየት አለበት ሲሉም አቶ ኤርስኖ ተናግረዋል።

በህፃናት መብት አያያዝና አጠባበቅ ዙሪያ የሚተኩር ሰነድ ያቀረቡት በጠቅላይ ፍርድ አቤቱታ መስማትና መወሰን ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ አብነዉ ናቸዉ።የቀረበዉን ሰነድ መነሻ በማድረግ የመድረኩ ተሳታፊያን በህፃናት መብትና ጥበቃ ዙሪያ ሀሳብ አስታያየት በመስጠት ሰፊ ውይይት ተደርጓል።በመድረኩ ማጠቃለያ አቶ ሀብታሙ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች በህፃናት መብት ጉዳይ ላይ በሚሰሩ ስራዎች ከህፃናት ጎን በመሆን በልዩ ትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ይድነቃቸዉ አንዳርጋቸው በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት አማራጭ የእርምት እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመድረኩ ማጠቃለያ ህፃናት በባህርያቸዉ በስነልቦናም ይሁን በአካል ከተጎዱ በኃላ ለማገገም ብዙ ጊዜ ስለሚወስድባቸዉ ልዩ ትኩረትና እንክብካቤ ልደረግላቸዉ እንደሚገባ አብራርተዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለዉ በህፃናት ጉዳይ ህጉን ከመተርጎም ባለፈ ስለህጉ ለማህበረሰባችን በሚገባ ዳኞች የማስረዳት ኃላፊነት እንዳለባቸዉ ገልጸዋል።የአንድ መስኮት አገልግሎትን ለማስፋት ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት አየሰሩ መሆናቸዉን አቶ ኤርስኖ ተናግረዋል።በመድረኩ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድቤት ባለድርሻ አካለት ፣የከተማ የመ/ደረጃ ፍርድቤት ፕሬዚዳንቶች ፣የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ፣መርማሪ ፖሊሶች ተሳተፊ ሆነዋል።

Image
president