Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ሥራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

‎ጥቅምት 2/2019

‎በማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት አቶ አንድአርጋቸዉ ይድነቃቸዉ የዘንድሮ ፍርድ ቤቶች የስራ ማስጀመሪያ የሆነዉ ጥቅምት አንድ ከባለፈዉ አመት የዳኞችና የጉባኤ ተሿሚዎች ጥቅማ ጥቅም በመመሪያ ቁጥር 74/2018 በተከበረበት ማግስት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት የፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 01/2016 አንቀጽ 59/2 መሠረት የክልሉ ፍርድ ቤቶች በየአመቱ ከነሐሴ አንድ እሰከ መስከረም ሰላሳ ድረስ ዝግ ሆኖ እንዲቆይ መወሰኑን ተናግረዋል።

‎በዚህ መሠረት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ጀምሮ እስከ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ድረስ ከነሀሴ 01 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 30 /2019 ዓ/ ም ድረስ በከፊል ዝግ ሆነዉ ለአስቸኳይ ጉዳይ ብቻ ተረኛ ችሎት ተመድቦላቸዉ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር መደበኛ ሙግቶች አለመከናወናቸዉን ተናግረዋል።

‎በሀገራችን ኢትዮጲያ ፍርድ ቤቶች ከሶስቱ የመንግስት አካላት አንዱ የሆነዉ ፍርድ ቤት ነፃና ገለልተኛ ተቋም በመሆን በህገመንግስቱ ሲቋቋም ለህዝብ የሚሰጡ የዳኝነት አገልግሎት ፈጣን፣ ተደራሽና ተገማች እንዲሁም ከአድሎ የጸዳ የፍትህ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባም አክለዋል።

‎በ2018 በጀት አመት የክልሉ ፍርድ ቤቶቻችን በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ በወንጀልና በፍትሐብሔር የቀረቡ መዝገቦችን ዉሳኔ በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ዉጤት የተመዘገበ አመት እንደነበር ጠቅሰዋል።

‎የተመዘገበዉን የተሻለ አፈጻጸም በ2019 በጀት አመት ይበልጥ ለማሻሻል ቃላችንን አድሰን በአዲስ ሞራል ወደስራ የምንገባበት ጊዜ መሆኑንም ገልጸዋል።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መስማትና መወሰን ስራሂደት አስተባባሪ አቶ ሸረፋ አሊ በበኩላቸው በባለፈዉ አመት የመዝገብ ክምችት መኖሩን ጠቅሰዉ በተቻለ መጠን የመዝገብ ክምችቱን በዉስን ዳኞች የማጣጣም ስራ እየተሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

‎የ2019 ዓ/ም የስራ ማስጀመሪያ እንደ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በርካታ አዳዲስ ዳኞች በመቀጠራቸዉ የቀጠይ 2019 ዓ / ም የዳኝነት ስራ አፈፃፀሙን ከባለፈዉ ዓመት የፍትህ አገልግሎቱን ቀልጣፋና ፍታሐዊ ለማድረግ አቅደዉ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

‎የሀላባ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሰኢድ አደም የዳኝነት ስራ ዳኞች የሚቀርብላቸዉን መዝገብ በመቀበል ለህዝብ የሚሰጡትን አገልግሎት ምን እንደሚመስል የመከታተል ስራ እንደሚሰሩ ጠቅሰዉ የዳኝነቱን ስራ በቅንነት፣ በታማኝነት እና በገለልተኝነት በተቀላጠፈ መልኩ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

‎አቶ ሰኢድ አክለወም የ2019 ዓ/ም የሀላባ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ የዳኝነት ስራ ከጥቅምት ሁለት ጀምሮ በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።

Image
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት አቶ አንድአርጋቸዉ ይድነቃቸዉ