የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የህዝብ ክንፍ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።
የካቲት 28/2017ዓ.ም ሆሳዕና ከተማ የተካሄደውን ፖናል ውይይት የመሩት የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርስኖ አቡሬ እና የክልሉ ም/ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት ወ/ሰንበት ናቸው።
ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ ኤርስኖ የውይይቱን አስፈላጊነት ሲገልፁ የህዝብ ክንፉንና ተጠቃሚውን ህብረተሰብ በፍ/ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እና ፍኖተ ካርታና በሚታዩ የአፈጻጸም ችግሮች ዙሪያ በመወያየትና ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት አሰራሩን ለማሻሻልና አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ በመውሰድ ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው።
አሳታፊ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በማዳበር ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ፍ/ቤቶችን ማጠናከር አለብን።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም መብትና ግዴታውን የተገነዘበ ህብረተሰብ ለመፍጠር እንዲሁም የቅሬታ አቀራረብ ስርዓትን በማጠናከር የተገልጋይን ህብረተሰብ ተጠቃሚነትን በማሣደግና አመኔታን በማትረፍ መልካም አስተዳደርን ማስፈን ነው ዓላማችን ብለዋል።
የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሣደግ በህገመንግስት የተሰጡትን መብቶች እንዲጠቀምበት በማስቻል መብትና ግዴታውን የተገነዘበ ህብረተሰብ መፍጠር አለብን ተብሏል።
ዳኞችና ባለሞያዎችን ማትጊያ የሚሆን የተጀመሩ የውሰጥ ዲሲፒሊን ደንቦችና መመሪያዎችን በአፋጣኝ የሚወጡበት ሁኔታ መኖር አለበት።
በፍርድ ቤቶች ፍኖተካርታ ዙሪያ ያደገ የህብረተሰብ ግንዛቤ እንዲኖረን እንዲሁም የተዘረጋ የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት ይኖራል ተብሎ ይታሰባል።
ህብረተሰቡ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጥ ለማበረታታት እንዲቻልና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከህብረተሰቡና ከህዝብ ክንፉ ጋር የሚደረግ ውይይት ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ተብሏል ።
046-55-62-112




