ቀን 23/12/2017
የማዕከላዊ ኢተዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመልካም እስተዳደር ችግሮች፣የችግሮቹ መንሴዎች እና መፍትሔዎች ዙሪያ ለዞንና ለልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በመስቀመጥ ተጠናቀቀ፡፡
መድረኩ በንግግር የከፈቱት የክልሉ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እንደገለጹት ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት አገልግሎት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ከብልሹ አሠራር ያልፀዳና በተለያየ መልኩ የሚገለጽ የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር ችግሮች የሚስተዋልበት በመሆኑ እነዚህን ችግሮች በቁርጠኝነት በመፍታት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ፈጣን፣ተደራሽና ከአድልዎ የፀዳ ተገማች የፍትህ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በክልሉ ፍርድ ቤቶች የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራሮችን መንስኤዎቻቸውን ላይቶ በማውጣት ችግሮቹ ለመፍታት በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራም ክቡር ፕሬዝደንቱ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ በክልል ፣በዞን፣ በልዩ ወረዳና ከተማ ፍርድ ቤቶች የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር፣ብልሹ አሰራርችግሮች፣የችግሮቹ መንስኤዋችና መፍትሔዎቹ ዙሪያ ከከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶች ጋር በመወያየት እንዲሁም ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ከወረደና ከከተማ ፍርድ ቤቶች ጋር በመወያየት አቅጣጫ በማስቀመጥ ለ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀን በማስመዝገብ የህብረተሰቡን የፍትህ እርካታን ለመጨመር በትኩረት መሥራት እንዳለባቸውም ፕሬዝደንቱ አስገንዝበዋል፡፡
ለውይይት መድረኩ በፍርድ ቤቶች ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርችግሮች፣የችግሮቹ መንስኤዎች እና መፍትሔዎች ላይ የሚያተኩር ሠነድ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ መኮንን ተሸለ ቀርቧል፡፡
ከመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረበውን ሠነድ መነሻ በማድረግ ለፍርድ ቤቶች የሚበጀተው በጀት አመዳደብ ሥርዓቱ ወጥነት የጎደለው በመሆኑ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ በመሆኑ ይህም የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ መምጣቱን የመድረኩ ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡
የሥራ ቦታን ምቹ ከማድረግ አንፃር ለፍርድ ቤቶች የመብራት መሠረተ-ልማት የተሌዩ ግብዓቶች አለሟሟላት፣የተቋም ግንባታ አለመኖር ፤የኑሮ ውድነት የዋጋ ንረት በተዘዋዋሪ ችሎት አገልግሎት አሠጣጥ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑን የመድረኩ ተሳታፊ ፕሬዝደንቶች ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም በዋስትና መብት ላይ ፈጣን ምላሽ አለመስጠት፣ማዘጋጀዎች ከሰነድ ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ መዘግየት፣የፍርድ ቤቶች የባለሙያ መደብ ከሌሎች ተቋማት አንፃር ሲታይ ዝቅተኛ መሆንና እንደ ክልል ቅጥር፣ዝውውር፣ደረጃ ዕድገት በመታገዱ አንድ ባለሙያ ሦስት የሥራ መደቦችን በውኪልና ዳርቦ እንዲሰራ በመደረጉ በፍርድ ቤቶቻችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጎልቶ እንዲታይ ምክንያት መሆኑን ከተለያዩ ፍርድ ቤቶች የተወጣጡ ፕሬዝደንቶች በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አንዳርጋቸው ይድነቃቸው ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየት ምላሽ ስሰጡ፡- ከበጀት ጋር የተያዘ ችግርን የዞን ፕሬዝደንቶች ከያሉበት አካባቢ አስፈፃጻዎች ጋር በመግባባት ለመፍታት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ በመጠቆም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ቁርጠኛ አመራር መሆን ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ከመደረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሲሰጡ የመልካም አስተዳደርን ጥያቄዎችን ለመፍታት በቅድሚያ ከራስ መጀመር እንደሚገባ በመግለጽ አንዳንድ ሥነ-ምግባር ጉድለት የሚታይባቸውን ዳኞችና የፍርድ ቤትን ስም የሚያጠፉ ጥቂት ጠበቆች መኖራቸውን በመጥቀስ በቀጣይ ከጠበቆች ጋር በመወያየት የማስተካከል ሥራ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መረጃና ማስረጃን መሠረት በማድረግ የሥነ-ምግባር ጉድለት የሚታይባቸውን ዳኞችና ባለሙያዎች ላይ የዕርምት ኤርምጃ ለመውሰድ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት የተመዘገበውን ውጤት በማስጠበቅ ለክፍተቶች መፍትሔ በማበጀት በ2018 በጀት ዓመት ጠንካራና ውጤታማ ሥራ ለመሥራት በጋራ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
046-55-62-112




