
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት መልዕክት
አቶ ኤርስኖ አቡሬ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በአዲስ መልክ መደራጀትን ተከትሎ የክልላችን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀላባ ክላስተር ከተደራጁት የክልል ተቋማት አንዱ ሆኖ በህገ መንግስትና በአዋጅ በተደነገገዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በአዲስ መልክ መደራጀትን ተከትሎ የክልላችን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀላባ ክላስተር ከተደራጁት የክልል ተቋማት አንዱ ሆኖ በህገ መንግስትና በአዋጅ በተደነገገዉ መሠረት በክልሉ የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን የተሰጠዉ ህግ ተርጓሚ የመንግስት አካል ነዉ፡፡
ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ሲሰጡ ነፃና ገለልተኛ በሆነ አግባብ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ህግና ማስረጃን መሰረት በማድረግ እልባት መስጠት የሚጠበቅባቸዉ በመሆኑ የዜጎችን ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን በማስጠበቅ ረገድ የፍርድ ቤቶች ሚና የጎላ በመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ለዉጤታማነቱ የሚኖረዉ አስተዋፅኦ ከፍ ያለ በመሆኑ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅዶ እየሠራ ይገኛል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በክልሉ ፍርድ ቤቶች የሚስተዋለዉን የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ፍኖተ- ካርታ ተግባራዊ በማድረግ የተለያዩ አዋጆችን፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን እያሻሻለ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ተገማች የሆነ ዳኝነት ለመስጠት የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ስለሆነ ህዝባችን ከጎን በመሆን ድጋፍ እንዲሰጠን እጠይቃለሁ ፡፡
የዳኝነት ተደራሽነትና ቅልጥፍናን ለማሳደግ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ በሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ስለምንገኝ የማዘመን ሥራ እየሠራን ስለሆነ የክልላችን ዳኞች ፣የህግ ባለሙያዎችና የአሰተዳደር ሠራተኞች ከተገልጋዩ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታትና ጠንክረን በመሥራት የህዝባችን የዳኝነት ጥያቄን በታማኝነት፣በቅንነትና በኃላፊነት ስሜት በመወጣት የህዝባችንን አመኔታ ለማትረፍ እንድንረባረብ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ከ 1985 ዓ.ም ጀምሮ ፍርድ ቤቱን የመሩት ፕሬዝዳንቶች
የማ/ኢ/ክ/ጠ/ ፍርድ ቤት ስራ ሂደቶችና ዳሬክቶሬቶች

መስማትና መወሰን ስራ ሂደት ዳይሬክተር

የተከላካይ ጠበቃ ጽ/ቤት ሃላፊ

የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ

የማ/ኢ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቃዲ


የመንግስት ኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዳሬክቶሬት

ስነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ዳሬክቶሬት

የልማት ዕቅድ ክ/ግ/ግ ዳይሬክቶሬት

የሰው ሀብት አስተዳደር ዳሬክቶሬት

ፋይናንስ ዘርፍ ዳሬክቶሬት

ኦዲት ዳሬክቶሬት

ሪከርድ እና ማህደር የስራ ሂደት
Latest News
Media
ከ 1985 ጀምሮ ፍርድ ቤቱን የመሩት ፕሬዝዳንቶች
![]() የማ/ኢ/ክ ጠቅላይ ፍርድቤት የአገልግሎት ዘመን ከጥቅምት 14/2014 ዓ/ም ጀምሮ - አስካሁን | ![]() የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን 8/06/06-ጥቅምት 24/ 2014 ዓ/ም | ![]() የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን ከህዳር 18/03/99-ታህሣስ 18/04/06 ዓ/ም |
![]() የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን ከ12/02/1996- 18/06/99 ዓ/ም | ![]() የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን ከየካቲት21/06/89-ጥቅምት 12//02/96 ዓ/ም | ![]() የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የአገልግሎት ዘመን ከ1985-የካቲት8/06/1989 ዓ/ም |
046-55-62-112













































